info@coffeesspices.gov.et | +251 46 221 0000
general

አመራሩ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ተግባራትን በሙሉ ትኩረት በቁርጠኝነት በመምራት ከግብ ማድረስ ይገባዋል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

August 12, 2026 8 Views
አመራሩ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ተግባራትን በሙሉ ትኩረት በቁርጠኝነት በመምራት ከግብ ማድረስ ይገባዋል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
አመራሩ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ተግባራትን በሙሉ ትኩረት በቁርጠኝነት በመምራት ከግብ ማድረስ ይገባዋል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ክልላዊ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ለማብሰር በክልሉ በመንግስትና ፓርቲ አመራር በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች በመከናወን ላይ የሚገኙ የ7ኛ ሳምንት ተግባራት ያሉበት ደረጃን በበይነ መረብ በመገምገም ለታለመው ግብ ስኬት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡
በስብሰባው የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ወገኔ ቡዙነህ፤ በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ለማብሰር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የደረሱበትን ደረጃ የተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ በክልሉ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሸፈን የሚያስችል አቅም በመገንባት እንደ ሀገር ወደ ተሟላ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነት ለመሸጋገር ለተያዘው ግብ ስኬት በልዩ ትኩረት በመሰራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህ ረገድ በክልሉ በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች በመከናወን ላይ ባሉ ተግባራት የ7ኛው ሳምንት አጠቃላይ አፈጻጸም አዳጊ ለውጦች መኖራቸውን የገመገሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ሆኖም ካለው አቅምና ከሚጠበቀው ውጤት አንጻር አሁንም በየመዋቅሩ ብዙ መስራት እንደሚገባ በአጽንኦት ገልፀዋል፡፡
እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የህልውና ጉዳይ መሆኑንም ጠቅሰው፤ አመራሩ አጀንዳው አንገብጋቢ ብቻ ሳይሆን የማይቀር መሆኑን በውል ተገንዝቦ የተጀመሩ ተግባራትን ብዝኃ ታታሪነትን ተላብሶ በሙሉ ትኩረት በቁርጠኝነት በመምራት ከግብ ማድረስ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ለስራዎች ውጤታማነት ተግባራትን በጠራ የአሰራር ስርዓት፤ በጠንካራ ተቋማዊ ማዕቀፍ መምራት ቁልፍ መሆኑንም ጠቁመው፤ በየደረጃው በመንግስትና ፓርቲ የተዘረጉ አደረጃጀቶችን እና የአሰራር ስርዓት ማዕቀፎችን ተጠቅሞ ለተያዘው ግብ ስኬት የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በክልሉ በፓርቲና መንግስት በተዘረጉ ምክር ቤት፤ የዐቢይ ኮሚቴ እና በቴክኒክ ኮሚቴዎች የሚመሩ ተግባራትን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ባለቤትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ስርዓት ዘርግቶ በጠንካራ ድጋፍና ክትትል ግብረመልስ በመስጠት ጭምር በመምራት ለውጤት ማብቃት እንደሚገባም አክለዋል፡፡
የተረጂዎችን መረጃ ከማጥራት እና ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ከማስተሳሰር አኳያ የሚታዩ መንጠባጠቦች በምንም ዓይነት ተቀባይነት የላቸውም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በየመዋቅሩ የተረጂዎች መረጃን በአግባብ ለይቶ ከፋይዳ ጋር የማስተሳሰር ስራን ሙሉ በሙሉ በተያዘው ሳምንት ማጠናቀቅ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ተረጂነትን በማስቀረት የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሸፈን የሚያስችል ተቋማዊ አቅም ለመገንባት በቀጣይም በየመዋቅሩ ደረጃቸውን የጠበቁ መጋዝኖችን ዝግጅት፤ ሳይበላሹ መቆየት የሚችሉ ሰብሎችን በመሰብሰብ ምላሽ መስጠት የሚያስችል የመጠባበቂ እህል ክምችት ማዘጋጀት ትኩረት የሚያሻው መሆኑን አስምረዋል፡፡
ከተፈናቃዮች ጋር ተያይዞም በማለቅ ላይ ያሉ ቤቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ መልሶ ማቋቋም እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በማቀላቀል ወደ ቀደም ህይወታቸው ለመመለስ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በቅርቡ የፀደቀውን የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ ደንብ እስከታችኛው መዋቅር በማውረድ፤ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ባሳተፈ መልኩ የመጠባበቂያ ፈንድ በመሰብሰብና በማስተዳደር ለተያዘው ግብ ስኬት መስራት እንደሚገባ በአጽንኦት ገልፀዋል።
በውይይቱ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላ በበኩላቸው፤ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን ለሚሰሩ ስራዎች ስኬታማነት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርና ጠንካራ የሆነ የአመራር ክትትል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአንዳድን መዋቅሮች አመራሩ ተግባራትን ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ በኃላፊነት ከመምራት አንጻር የሚታዩ ክፍተቶች ልታረሙ ይገባል ያሉት ኃላፊው፤ የሚቀርቡ መረጃዎችም በአግባብ ተጣርተውና ተቋማዊ በሆነ አግባብ ተገምግመው ልቀርቡ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልፀዋል።
በውይይቱ የክልሉ የአደጋ ስጋት ምክር ቤት አባላት፤ የፓርቲ ኃላፊዎች፤ የዞን አስተዳዳሪዎች እና የሬጂዮ ፖሊስ ከተሞች ከንቲባዎች ተሳትፈዋል፡፡
Share this article: