info@coffeesspices.gov.et | +251 46 221 0000
General

በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርታማነትን ለማጎልበት የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል

June 15, 2026 34 Views
በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርታማነትን ለማጎልበት የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል
በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርታማነትን ለማጎልበት የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል
ዲላ፤ ሐምሌ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን ለማጎልበት የተጀመረው ሥራ እንደሚጠናከር የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ የ2018/19 የመኸር አዝመራ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በዲላ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በክልሉ በተያዘው የመኸር እርሻ በቋሚና በዓመታዊ ሰብሎች ከ909 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ይለማል።
በክልሉ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ሥራ በተያዘው የመኸር ወቅትም በትኩረት መስራቱ ይቀጥላል ብለዋል።
ባለፈው ዓመት የመኸር ወቅት ከ855 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማረስ ከታቀደው በላይ ምርት መሰብሰቡን አስታውሰው፣ በ2018/2019 የመኸር ወቅትም በቋሚና ዓመታዊ ሰብሎች ከ909 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንደሚለማ አረጋግጠዋል።
Share this article: