info@coffeesspices.gov.et | +251 46 221 0000
General

በክልሉ አዳዲስ የግብርና ኢኒሼቲቮች በላቀ ደረጃ በመፈፀም የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል - አቶ ኡስማን ሱሩር

December 13, 2025 17 Views
በክልሉ አዳዲስ የግብርና ኢኒሼቲቮች በላቀ ደረጃ በመፈፀም የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል - አቶ ኡስማን ሱሩር
በክልሉ አዳዲስ የግብርና ኢኒሼቲቮች በላቀ ደረጃ በመፈፀም የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል - አቶ ኡስማን ሱሩር
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2/2018 ዓ.ም፣ (ግብርና ሚኒስቴር)
በክልሉ አዳዲስ የግብርና ኢኒሼቲቮች በላቀ ደረጃ በመፈፀም የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደተቻለ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ገለጹ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከጉራጌ፣ ከየም ዞንና ከቀቤና ልዩ ወረዳ ሁሉም መዋቅሮች ለተውጣጡ 2 ሺህ ለሚሆኑ የግብርና ልማት ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በወልቂጤ ከተማ እየተሰጠ ነው።
አቶ ኡስማን ሱሩር በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ አዳዲስ የግብርና ኢኒሼቲቮች በላቀ ደረጃ በመፈፀም የአርሶ አደሩን ተጠቀሚነት ማሳደግ ተችሏል።
በትንሽ መሬት ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ቴክኖሎጂ እና ኢኒሼቲቭ ተቀርፆ በሁሉም አካባቢ በመተግበርና በማስፋፋት ከፍጆታ አልፎ ለገበያ የሚያመርት አርሶ አደር ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ባለፉት ተከታታይ ቀናት ከእጅ ወደ አፍ የሆነ የግብርና የአመራረት ስርዓት በመቀየር ዘመናዊ ግብርናን እውን ለማድረግ አርሶ አደሩን ወደ አንድ ምዕራፍ ከፍ የሚያደርግ ስልጠና ለልማት ጣቢያ ሠራተኞች እየተሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል።
ስልጠናው ባለፉት አመታት ግብርናውን በማዘመን የተገኙ ውጤቶችን የምናሰፋበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ግብርናን ከፍጆታ መር በማሸጋገር የወደፊት የማህበረሰብና የቤተሰብ ብልፅግና ለማረጋገጥ መነሳሳት የሚፈጠር መሆኑን አቶ ኡስማን አስታውቀዋል።
ስልጠናው ስኬቶችን በማስፋት ጉድለቶች በማረምና መልካም ተሞክሮዎች በማጠናከር ልማቱ ወደ ሁሉም ቀዬ እንዲደረስ የጎላ አስተዋፅኦ እንዳለው አቶ ኡስማን መናገራቸዉን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
Share this article: